የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር 60ኛው ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አዉደ ርዕይ አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ
የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ከተመሰረተ 1954ዓ.ም ጀምሮ በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ በታካሚዎች ደህንነት እና በአጠቃላይ በህክምናው ዘርፍ ቁልፍ ሚና በመጫወት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ማህበር ነው፡፡ የማህበሩ ራዕይ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችል ጤናማና የበለፀገ ማህበረሰብ ማየት ነው፡፡ ይህንን እውን ለማድረግ ይረዳ ዘንድም ከሚመለከታቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች በተለይም የጤና ሚኒስትርን ጨምሮ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲሁም ከስፔሻሊቲ ሶሳይቲዎች እና ከማህበሩ አባላት ጋር በመሆን…